በኮሮናቫይረስ ሀገራት የጉዞ ገደብ እያደረጉ ነው

  • ቪኦኤ ዜና

የዓለም ጤና ድርጅት ዋና ዳይሬክተር ዶ/ር ቴድሮስ አድሃኖም

"ኮሮናቫይረስ ወረርሽኝ ነው" - የዓለም የጤና ድርጅት

በዓለም ዙርያ ያሉት መንግሥታት የኮሮናቫይርስ በግዛቶቻቸው መዛምትን ለመገደብና ከውጭም እንዳይገባ ለመግታት በሚያደርጉት ጥረት የጉዞ ገደብች እያደረጉ ነው።

የዩናይናይትድ ስቴትስ ፕሬዚዳንት ዶናልድ ትረምፕ ትናንት ማታ በቴሌቪዥን ባደረጉት ንግግር፣ በቅርቡ የአውሮፓን ሸንገን አካቢቢ የጎበኙ የውጭ ሀገር ተወላጆች ዩናይትድ ስቴትስ እንዳይገቡ አግደዋል። አስተዳደቸራው ኢኮኖሚን አስመልክቶ ስለሚወስደው ዕርምጃም አንስተዋል።

የሀገሪቱ ዲሞክራስያዊ ፓርቲ መሪዎች በሀገሪቱ ስፊ የምርመራ ተግባር ለማካሄድ የሚያስችል ሁኔታ ለመፍጠር በቂ ጥረት አልተደርገም በማለት መንቀፋቸው አልቀረም። ነፃ ምርመር እንዲደረግና ሰዎች የመታመም ስሜት ከተሰማቸው ወደ ሥራ እንዳይሄዱ ለማበራታት ክፍያ እንዳይቋራጥባቸው የሚያስችል ህግ የማውጣት ሃስብ አቅርበዋል።

ሳውዲ አረብያ የአውሮፓ ህብረት፣ ህንድ፣ ፕኪስታን፣ ኢትዮጵያ፣ ሱዳንና ኬንያ ወደ ሚገኙባቸው ሀገሮች ላለመጓዝና ከነዛም እንዳይገቡባት አግዳለች።

ኤል ሳልቫዶር ሁሉም የውጭ ሃገራት ተወላጆች እንዳይገቡባት አግዳለች። ጓተማላ ከአውሮፓ፣ ከኢራን፣ ከቻይና፣ ከሰሜንና ከደቡብ ኮርያ ወደ ግዛትዋ እንዳይገቡ አግዳለች።

የዓለም የጤና ድርጅት ኮሮናቫይረስ ወረርሽኝ ነው ሲል ትላንት በኦፊሴል አስታውቋል።