ኮቪድ-19 በህንድ

  • ቪኦኤ ዜና

ህንድ ውስጥ ባለፉት 24 ሰዓታት ውስጥ 28ሺህ 701አዲስ ለኮሮናቫይረስ የተጋለጡ ሰዎች መገኘታቸው ተገለፀ። ዓለም አቀፉ ወረሽኝ፣ ባለፈው ህዳር ወር ገደማ ከጀመረበት ጊዜ አንስቶ፣ ህንድ በቫይረሱ በሽተኞች ብዛት፣ ከዩናይትድ ስቴትስና ከብራዚል ቀጥላ ሦስተኛውን ቦታ ይዛለች። በርካታ የክፍላተ-ግዛት ባለሥልጣኖች፣ አላልተውት የነበረውን የመንቀሳቅስ ገደብ እንደገና እያጠብቁ ነው።

ህንድ ውስጥ በኮቪድ-19 ምክንያት የሞቱ 23,174 ከቫይረሱ ያገገሙ 553,471 መሆናቸውን የጆንስ ሆፕኪንስ ዩኒቨርስቲ መረጃ አመልክቷል።