ለዓለም አቀፍ ሽልማት የበቃው ትንሹ ባለ ግዙፍ ሕልም ኩባንያ

የድርጅቱ ተባባሪ መሥራች እና ሥራ አስፈጻሚ ሊቀመንበር ቅዱስ አስፋው

ለሰው ልጆች ጤና ጠንቅ ሊሆኑ የሚችሉ በየሥፍራው የተጣሉ የፕላስቲክ ተረፈ ምርቶችን ተጠቅሞ የግንባታ ግብአቶችን የሚያመርት የቴክኖሎጂ ኩባንያ ነው።

"ኪዩቢክ" ይሰኛል። ገና በምሥረታው የመጀመሪያ እርከን ላይ የሚገኘው ኩባንያ በቅርቡም ለአንድ ዓለም አቀፍ ከፍተኛ ሽልማት እና እውቅና በቅቷል። አሕጉረ አፍሪካን ለማልማት እና ለማሳደግ ‘ሁላችንም በየበኩላችን ልናደርግ የምንችለው ነገር አለ’ ይላል።

Your browser doesn’t support HTML5

ለዓለም አቀፍ ሽልማት የበቃው ትንሹ ባለ ግዙፍ ሕልም ኩባንያ

የድርጅቱ ተባባሪ መሥራች እና ሥራ አስፈጻሚ ሊቀመንበር ጋብዘን አወያይተናል። ኩባንያቸው ኪዩቢክ ስለያዘው ታላቅ ውጥን እና ሕልም፣ ለእውቅና ስለ በቁበት ሥራቸው እና ስለመጡበት መንገድ ያወጉናል።

ሙሉውን ምልልሳችንን ከዚህ ያድምጡ።