የሰሊጥ ግብይት በሱዳንና በኢትዮጵያ የግጭት መነሻ እንደሆነ አንድ ጥናት አመለከተ

ዶ/ር አቤል አባተ

Your browser doesn’t support HTML5

የሰሊጥ ግብይት በሱዳንና በኢትዮጵያ የግጭት መነሻ እንደሆነ አንድ ጥናት አመለከተ

የሰሊጥ ምርት እና ግብይት፣ በኢትዮጵያ እና በሱዳን መካከል፣ እንዲሁም በሁለቱም አገሮች የውስጥ አወዛጋቢ ጉዳዮች ዙሪያ የግጭት መንሥኤ እየሆነ እንደሚገኝ፣ አንድ ጥናታዊ ጽሑፍ አመለከተ፡፡

“The ‘conflict economy’ of sesame in Ethiopia and the Sudan” በሚል ርእስ የወጣውን ጥናት ከአዘጋጁት ሁለት ምሁራን አንዱ ዶ/ር አቤል አባተ ደምሴ፣ “የሰሊጥ ግብይት በሱዳንና በኢትዮጵያ የውስጥ እና የውጭ ጉዳዮች ላይ ተጽእኖ ፈጥሯል፤” ይላሉ፡፡

ዶ/ር አቤል፣ ላለፉት አራት ዓመታት፣ በለንደን በሚገኘው ዓለም አቀፍ የፖሊሲ ተቋም(ቻተም ሃውስ) የሮያል ዓለም አቀፍ ጉዳዮች ተቋም የምርምር ባልደረባ ሆነው በመሥራት ላይ ናቸው፡፡ ምሁሩ በጥናታቸው ላይ እንዳመለከቱት፥ የመንግሥት ኀይሎች፣ የአካባቢ ልሂቃንና ሚሊሻዎች በሰሊጥ ምርት እና ንግድ ላይ ቁጥጥር ለማድረግ እየተፎካከሩ ናቸው፡፡

ፖሊሲ አውጪዎች፣ በኢትዮጵያ እና በሱዳን መካከል ያለውን ትስስር ፖለቲካዊ፣ ኢኮኖሚያዊ እና የግብርና ለውጦችን በማስተካከል ዘላቂ ሰላምን ለማምጣት፣ መሠረታዊ እና ተለዋዋጭ ፖሊሲዎችን መቅረጽ እንዳለባቸው መክረዋል፡፡

ፖሊሲ አውጭዎቹ መደበኛ ያልሆነ የንግድ ልውውጥን እንዲደግፉና ከታች ወደ ላይ ለአካባቢያዊ አብሮ መኖርና ትብብር ኹኔታዎችን እንዲያመቻቹ ጥናቱ ምክረ ሐሳብ ማቅረቡን ከአዘጋጆቹ አንዱ ዶ/ር አቤል አባተ ተናግረዋል፡፡ ዝርዝሩን ከተያያዘው ፋይል ይከታተሉ።

ዝርዝር ዘገባውን ከተያያዘው ፋይል ይከታተሉ።