"ቀልዶች የልብ አውጥቶ ለመናገርና አንጀት ለማራስ የሚያስችሉ ጥበቦች ናቸው"ዶ/ር አብርሃም ዓለሙ

ዶ/ር አብርሃም ዓለሙ የሥነ ጹሑፍና ፎክሎር ተመራማሪ

በኢትዮጵያ መንግሥት ላይ የተቀለዱ ቀልዶችን አሰባስበዋል፤በቃለ ምልልሱም ተካቷል

ቀልድ በአንድ ማኅበረሰብ ውስጥ አይነኬ የሚባሉ ፓለቲካዊ፣ኃይማኖታዎ፣ጾታዊ እንዲሁም በመደበኛ ሁኔታ ቢነገሩ ሊያስቆጡና ግጭትን ሊቀሰቅሱ የሚችሉ ሐሳቦች ያለ አንዳንች ስጋት የሚነገርበት ጥበብ ነው፡፡ ሰዎች አደባባይ ወጥተው ሐሳባቸውን መናገር ሲያቅታቸውም በየቤቱ በነጻነት የሚተነፍሱበት የሰውን ልጅ ከአዕምሮአዊ ጭንቀት የሚያወጣ ማስተንፈሻ ነው፡፡

ዶ/ር አብረሃም ዓለሙ በአዲስ አበባ ዩኒቨርስቲ በኢትዮጵያ ሥነ ጹሑፍና ፎክሎር ክፍለ ትምሕርት መምሕርና የክፍለ ትምሕርቱ ኃላፊ ነበሩ፡፡ አሁን እዚህ ዩናይትድ ስቴትስ ካሊፎርኒያ ስቴት ዩኒቨርስቲ ሳንበርናንዲኖ ውስጥ የአፍሪካ ምርምር ተቋም ውስጥ መምሕር ናቸው፡፡

ዶ/ር አብርሃም ከሥነ ሕዝብ ጥበብ ውስጥ አንዱ የኾነው ቀልድ በአንድ ማኅበረሰብ ውስጥ ስለሚኖረው ማኅበራዊ፣ፖለቲካዊና፣ባሕላዊ ፋይዳ ሲናገሩ፤ “ቀልድ እንዲሁ ለማሳቅ በዋዛ ፈዛዛ የሚነገር ይመስላል፡፡ግን ማሳቁ እና ማዝናናቱ በወስጡ ይዞ የሚገኘውን መራር እውነት ለማሳፈን የሚያገለግል ብቻ ነው፡፡ልክ ለሕፃናት የሚቀርቡ መድኃኒቶች ስኳር ቅብ እንደሚኾኑት ቀልዶችም ከማዋዛት፣ማዝናናትና ማስደሰት ጀርባ ትልቅ ቁም ነገር የያዙ እጅግ በጣም ኃያል ባሕላዊ መሳሪያዎች ናቸው”ይላሉ፡፡

“በዚህ ዘመን የኢትዮጵያ ሕዝብ ጤንነቱንና ማኅበረሰባዊ ሕልውናውን ጠብቆ ከሚገኝባቸው ባሕላዊ መሳሪያዎች አንዱ ቀልድ ነው” የሚሉት ዶ/ር አብርሃም ዓለሙ በዚሁ ጉዳይ ላይ ከጽዮን ግርማ ጋር ቆይታ አድርግዋል፡፡

ዝርዝሩን ከተያያዘው ድምጽ ያድምጡ፡፡

Your browser doesn’t support HTML5

"ቀልዶች የልብ አውጥቶ ለመናገርና አንጀት ለማራስ የሚያስችሉ ጥበቦች ናቸው"ዶ/ር አብርሃም ዓለሙ