በዓየር ንብረት ለውጥ ላይ በፓሪስ የሚደረግ ጉባኤ

በዓለም ዙሪያ የተለያዩ አገሮች ባለሥልጣናት በመጪው በያዝነው የሕዳር ወር መገባደጂያ ፓሪስ ላይ ለሚከፈተውና ለሁለት ሳምንታት ለሚዘልቀው በዓየር ንብረት ጠባይ ለውጥ ላይ የሚያተኩር ጉባኤ ደፋ ቀና ይዘዋል።

ጉባኤው ወደ ከባቢ ዓየር በሚለቀቀው የካርቦን መጠን ላይ በሕግ ገደብ የሚያደርግ ሁሉን አቀፍ ስምምነት ከሁለት አሥርታት ያልተቋረጠ ድርድር በኋላ በመጨረሻው ይደረስ ይሆናል፤ የሚል ተሥፋ አሳድሯል።

ዚልቲካ ሆከ(Zilatica Hoke) ከዋሽንግተን ዲሲ ባጠናቀረችው ዘገባ እንዳመለከተችው፤ በትላንትናው ዕለት በፓሪስ ዋና የመነጋገሪያ አጀንዳ ሆኖ የቀረበው ይህ ጉዳይ በዩናይትድ ስቴትስም ተመሳሳይ ሥፍራ ተሰጥቶት ነበር። ዝርዝሩን አሉላ ከበደ ይዞ ቀርቧል። ከተያያዘው የድምጽ ፋይል ያዳምጡ።

Your browser doesn’t support HTML5

በዓየር ንብረት ለውጥ ላይ በፓሪስ የሚደረግ ጉባኤ