ዛሬ ማክሰኞ ዋና ከተማዋ ላይ ውጊያ የተቀሰቀሰው በፓርላማው የተሾሙት ጠቅላይ ሚኒስትር ፋቲ ባሻጋ ለመልቀቅ ፈቃደኛ አልሆን ካለው ተቀናቃኝ ቡድን ላይ የአስተዳደሩን ሥልጣን ለመውሰድ ሙከራ ማድረጋቸውን ተከትሎ መሆኑ ተዘግቧል።
ሁለቱ ተቀናቃኝ ቡድኖች ለሁለት ወር ያህል ከተፋጠጡ በኋላ አዲሱ ጠቅላይ ሚኒስትር ትናንት ሌሊቱን ትሪፖሊ የገቡ ሲሆን መዲናዋን ከባድ ተኩስ ሲያናውጣት ከጥቂት ሰዓት በኋላ መውጣታቸውን የጠቅላይ ሚኒስትሩ ጽህፈት ቤት አመልክቷል።
ቀውሱ ለሁለት ዓመታት ያህል አንጻራዊ ሰላም ያገኘችውን ሀገር ወደተራዘመ ውጊያ ሊመልሳት ይችላል የሚል ሥጋት ፈጥሯል።