በእየሩሳሌሙ አል አቅሳ መስጊድ ግጭት 152 ሰዎች ቆስለዋል

በእየሩሳሌም ውስጥ በሚገኘው አል አቅሳ መስጊድ ቅጥር ግቢ ውስጥ በፍልስጥኤማውያን እና በእስራኤል ፖሊሶች መካከል በተፈጠረ ግጭት ቢያንስ 152 ፍልስጥኤማውያን መቁሰላቸውን የህክምና እርዳታ ሰራተኞች ገለጹ እአአ ሚያዚያ 15/2022

በእየሩሳሌም ውስጥ በሚገኘው አል አቅሳ መስጊድ ቅጥር ግቢ ውስጥ በፍልስጥኤማውያን እና በእስራኤል ፖሊሶች መካከል በተፈጠረ ግጭት ቢያንስ 152 ፍልስጥኤማውያን መቁሰላቸውን የህክምና እርዳታ ሰራተኞች ገለጹ እአአ ሚያዚያ 15/2022

በእየሩሳሌም ውስጥ በሚገኘው አል አቅሳ መስጊድ ቅጥር ግቢ ውስጥ በፍልስጥኤማውያን እና በእስራኤል ፖሊሶች መካከል በተፈጠረ ግጭት ቢያንስ 152 ፍልስጥኤማውያን መቁሰላቸውን የህክምና እርዳታ ሰራተኞች ገለጹ።

ግጭቱ የተከሰተው ዛሬ አርብ ከንጋት በፊት በሺሕዎች የሚቆጠሩ ለረመዳን ጸሎት በተሰባሰቡበት ሰዓት ሲሆን ፖሊሶች ግጭቱን አስቁመናል፤ ብዙ መቶ ተጠርጣሪዎችን አስረናል ብለዋል።

መስጊዱም ለወትሮው የአርብ ሶላት ክፍት መሆኑን ገልጸዋል። ስማቸው እንዳይገለጽ የጠየቁ ዕማኞች በበኩላቸው ጥቂት ፍልስጣኤማውያን ፖሊሶች ላይ ድንጋይ ሲወረውሩ ፖሊሶች መስጊዱ ግቢ ገቡ ብጥብጡ ተባባሰ ብለዋል።

የፍልስጥኤም ቀይ ጨረቃ አጣዳፊ እርዳታ ሰራተኞች 152 ቁስለኞች አክመናል አብዛኞቹ የተመቱት በጎማ ጥይት እና በማስደንገጫ ፈንጂ ወይም በዱላ የተደበደቡ ናቸው ብሏል።

በኢንተርኔት በተሰራጩ ምስሎች ፍልስጥኤማውያን በፖሊሶች ላይ ድንጋይ ሲወረውሩ እና ፖሊሶች አስለቃስ ጋዝ እና ማስደንገጫ ፈንጂ ሲተኩሱ መስጊዱ ውስጥ ተደብቀው ይታያሉ።

በሙስሊሞችም በአይሁድም ዘንድ ቅዱስ ተደርጎ በሚታየው ስፍራ ባለፈው ዓመት የተፈጠረውን ግጭት ተከትሎ በጋዛ ሰርጥ በእስራኤል እና በሃማስ ታጣቂዎች መካከል ለአስራ አንድ ቀናት የዘለቀ ውጊያ መካሄዱ ይታወሳል።