በሺዎች የሚቆጠሩ ሴቶች ብቻ በተሳተፉበት ትዕይንተ ሕዝብ ላይ፣ ብሄረሰቡ ከነበረበት የደቡብ ህዝቦች እና ብሄረሰቦች ክልል ተነጥሎ በአፋጣኝ ክልልነት ዕወቅና እንዲሰጠው የሚጠይቁ መፈክሮች እና መልዕክቶች ተሰምተውበታል፡፡
ሃዋሳ —
ሲዳማ 10ኛ ክልል ሆኖ ዕወቅና ሲያገኝ በስራ ላይ ይውላል ተብሎ የተነገረለትን ቀይ ነጭ እና ሰማያዊ ቀለም ፊታቸው ላይ የተቀቡ ወጣቶች ‹‹ህገ-መንግስታዊ ›› መሆኑን የጠቀሱት ጥያቄ መልስ እንዲያገኝ ሲጠይቁ አርፍደዋል፡፡
የሲዳማ ዞን ምክር ቤት ሀምሌ 11/2010 ዓመተ ምህረት ባደረገው ስብሰባ ዞኑ ክልል እንዲሆን ለመጠየቅ በሙሉ ድምጽ መስማማቱ ይታወሳል፡፡እሱን ተከትሎ ጠካቲት 14/2011 ወንዶች ብቻ የተሳተፉበት ትዕይንተ ሰልፍ በሀዋሳ ከተማ ተካሄዷል፡፡
በዛሬው ትዕይንተ ሰልፍ ላይ የተገኙትየደቡብ ብሔር ብሔረቦች እና ሕዝቦች ክልል ፕሬዝዳንት አቶ ሚሊዮን ማቴዎስ እና የሐዋሳ ከተማ ከንቲባ አቶ ስኳሬ ሾዴ ጥያቄው ሕገ-መንግሥታዊ ነው፣ ተግባራዊ እንዲሆን ጥረት እንደሚያደርጉ ቃል ሲገቡ ተሰምተዋል፡፡
በደቡብ ብሄራዊ ክልላዊ መንግስት ከሚገኙ ከ50 በላይ የሆኑ ብሄርእና ብሄረሰቦች መካከል አንዱ የሆነው የሲዳማ ብሄረሰብ የሕዝብ ቁጥሩ ከ5 ሚሊየን በላይ እንደሆነ ይገመታል፡፡
Your browser doesn’t support HTML5