ሀዋሳ —
በደቡብ ክልል ደቡብ ኦሞ ዞን ዳሰነች ወረዳ በተነሳ የኮሌራ ወረርሽኝ ከ40 በላይ ሰዎች ሳይሞቱ እንዳልቀሩ የአከባቢው ነዋሪዎች በስልክ ለአሜሪካ ድምጽ ተናገሩ።
መንግሥት በቂ የጤና ድጋፍ እያደረገ አለመሆኑን ገልጸው ሃገርቀፍ ድጋፍ ወይንም የዓለምቀፍ ድርጅቶች ጣልቃ ካልገቡ በርካታ ህዝብ በወረርሽኙ ሊያልቅ እንደሚችል ጠቁመዋል።
የክልሉ ጤና ቢሮ ኃላፊ አቶ አቅናው ካውዛ በበኩላቸው በጤና ተቋም መጥተው ህይወታቸው ያለፉ ሰዎች 11 መሆናቸውን ገልጸዋል።
ለተጨማሪ የተያያዘውን የድምፅ ፋይል ያዳምጡ።
Your browser doesn’t support HTML5