የቻይና የኢኮኖሚ ኃላፊ ም/ጠቅላይ ሚኒስትር ሉሂ ለሁለተኛ የድርድር ዙር በያዝነው ወር ወደ ዩናይትድ ስቴትስ ይጓዛሉ።
ዋሺንግተን ዲሲ —
የቻይና የኢኮኖሚ ኃላፊ ም/ጠቅላይ ሚኒስትር ሉሂ ለሁለተኛ የድርድር ዙር በያዝነው ወር ወደ ዩናይትድ ስቴትስ ይጓዛሉ። በሁለቱም በኢኮኖም የበለፀጉ ሀገሮች መካከል ለሚካሄደው የንግድ ጦርነት መፍትሄ ለማግኘት ነው የሚደራደሩት።
የንግድ ሚኒስቴር ቃል አቀባይ ጋኦ ፈነገ ዛሬ ቤዢን ላይ ለጋዜጠኞች በሰጡት መግለጫ ሊሃ እአአ ጥር 30 እና 31 ቀናት ዋሺንግተን ይቆያሉ ብለዋል። የዩናይትድ ስቴትስ የገንዘብ ሚኒስትር ስቲቭን ምኑቺንና የንግድ ተወካይ ሮበርት ላይትዘር ባደረጉላቸው ግብዣ መሰረት ነው ወደ ዋሺንግተን የሚመጡት።