የአፍሪካ ቀንድ ቀጠና ኢትዮጵያ ውስጥ ካለው ጦርነት በተጨማሪ በተስተጓጎለው የሶማሊያ ምርጫ እና በሱዳን መፈንቅለ መንግስት እየተናጠ ይገኛል፡፡ ይህ የቻይና እርምጃ ቻይና በቀጠናው ፖለቲካ ላይ እና በወታደራዊ ጉዳዮች ላይ ከፍተኛ የሆነ ፍላጎት እንዳላት ያመላከተ ነው፡፡
የቻይናው የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ዋንግ ዪ “የቀጠናው እድል በብርቱ በሕዝቦቹ እጅ እንዲሆን ተመጣጣኝ የሆነ የማማካረ እና እንቅስቃሴ ልናደረግ ያሻል፡፡ በዚህ ቀጠና የሚኖሩ ሰዎች በአፍሪካ ቀንድ የጸጥታ ጉዳይ ላይ ስብሰባ ሊያዘጋጁ ይገባል፡፡ ፖለቲካዊ ስምምንት ላይ ለመድረስ፣ ድርጊቶችን ለማስተባበር ቻይን በውጭ ጉዳይ መስሪያ ቤቷ አማካኝነት ይህን ሁኔታ የሚያግዝ እና አስፈላጊውን ድጋፍ የሚያደርግ የአፍሪካ ቀንድ ልዩ ልዑክ ትሾማለች፡፡” ሲሉ የሃገራቸውን ፍላጎት አስታውቀዋል፡፡
Your browser doesn’t support HTML5