ቻይና ሠራዊትና ሀኪሞችን ለክትባት አሰማራች

  • ቪኦኤ ዜና

ፎቶ ፋይል፦ ሻንጋይ፣ ቻይና መጋቢት 29/2022

ቻይና በአገሯ እያገረሸ የመጣውን የኮቪድ-19 ወረርሽኝ ለመቋቋም ሻንጋይ በተባለው ክፍለ ግዛቷ የሚኖሩትን 26ሚሊዮን ሰዎች በሙሉ በአንድ ጊዜ ለማስከተብ ሠራዊቷንና በሺዎች የሚቆጠሩ የጤና ሠራተኞችን ማሰማራቷ ተገለጸ፡፡

በዚህ መጠን በአንድ ጊዜ ለህዝብ የጤና አገልግሎት ምላሽ ሲሰጥ ይህ የመጀመሪያው ነው ተብሏል፡፡

ብዙዎቹ ነዋሪዎች ከለበሱት የሌሊት ልብስ (ፒጃማ) ጋር ከእንቅልፋቸው እንዲነሱ የተቀሰቀሱ ሲሆን ቤታቸው የኮቪድ-19 ምርመራ የተደረገላቸው መሆኑን ተመልክቷል፡፡

ትናንት በተደረገው ምርመራ ሻንጋይ ውስጥ ቫይረሱን ማስተላለፍ የሚችሉ 8ሺ581 ሰዎች ያሉ ሲሆን ለቫይረሱ የተጋለጡ 425 ሰዎች መኖራቸው ተመልክቷል፡፡

ምንም እንኳ የሥርጭቱ መጠን ከሌላው ዓለም ጋር ሲነጻጸር ዝቅተኛ መሆኑን ቢገለጽም የአገሪቱ ፕሬዚዳን ዚ ጂፒንግ በአገሪቱ እንደገና በማገርሸት ላይ የሚገኘው ቫይረስ በመቀልበስ ሙሉ ለሙሉ እንዲጠፋ የሚያዘው ፖሊሲ ተግባራዊ እንዲደረግ ማስታወቃቸው ተመልክቷል፡፡