ዋሺንግተን ዲሲ —
ቻይና 10,000 የኮሮናቫይረስ በሽተኞች እንዳሉ ማረጋገጧን ገልጻለች። ቫይረሱ ቻይና የገባው ከጥቂት ወራት በፊት ሲሆን እስካሁን ባለው ጊዜ 213 ሰዎች መሞታቸው ታውቋል።
የዓለም የጤና ድርጅት በዓለም ዙሪያ የተዛመተው ኮሮናቫይረስ በዓለም ደረጃ አስቸኳይ የጤና ሁኔታ ነው ሲል አውጇል። የተባበረ ዓለምቀፍ ምላሽ እደሚያስፈልገውም የጤናው ድርጅት ጠቁሟል።
የትረምፕ አስተዳደር አሜሪካውይን ወደ ቻይና እንዳይጓዙ አስጠንቅቋል።
ብሪትንያ ውስጥ የአንድ ቤተሰብ አባላት የሆኑ ሁለት የኮሮናቫይረስ በሽተኞች መገኘታቸው ተረጋግጧል። ሁለቱ በሽተኞች ከሀገሪቱ ብሄራዊ የጤና አገልግሎት ልዩ ህክምና እየተደረገላቸው መሆኑን ዋናው የብሪታኒያ የህክምና ኃላፊ ክሪስ ዊትኒ ተናግረዋል።
ህንድና ፊሊፒኒስም ለመጀምሪያ ጊዜ የኮኖናቫይረስ በሽተኞች እንደተገኙባቸው ገልጸዋል። አውስትራልያ፣ ካናዳ፣ ፊንላንድ፣ ጀርማን፣ ሆንግ ኮንግ፤ ጃፓን፣ ኔፓል፣ ሲንጋፖር፣ ደቡብ ኮርያ፣ ታይላንድ፣ የተባበረው የአረብ ኤሚሬቶችና ቬትናምም የኮሮናቫይረስ በሽተኞች እንዳሉባቸው አስታውቀዋል።