በምጣኔ ሃብት ከዓለም ሁለተኛዋ ቻይና - ዘንድሮ ከገጠማት አነስተኛ እድገትና ከዩናይትድ ስቴትስ ጋር የንግድ ንትርክ ውስጥ በመሆኗ ከባድ ፈተና ይጠብቃታል ሲሉ የሃገሪቱ ጠቅላይ ሚኒስትር ሊ ኪኪያንግ አስጠነቀቁ።
ዋሺንግተን ዲሲ —
ጠቅላይ ሚኒስትሩ 3000 ሺህ ልዑካን ለተገኙበት ብሄራዊው የሕዝብ ምክር ቤት ባደረጉት ዓመታዊ ንግግር ቤይጂንግ በዚህ ዓመት የምትጠብቀው የኢኮኖሚ እድገት - ከ 6 እስከ 6 ነጥብ 5 በመቶ ይሆናል ሲሉ አስረድተዋል። ብዙ ሃገሮች ይህን የእድገት መጠን ለማስመዝገብ የሚቸገሩ ሲሆን፡ ለቻይና ግን ከ 30 ዓመታት ወዲህ ዝቅተኛው እንደሚሆን ተገምቷል።
የቻይና ኮሚኒስት አመራር ሀገሪቱን ከዚህ ከባድ የኢኮኖሚ ማዕበል ሊያወጣ እንደሚችል እምነታቸው መሆኑን ግን ጠቅላይ ሚኒስትር ሊ ኪኪያንግ አስታውቀዋል።