የቻይናና ሩሲያ የጠፈር ወታደራዊ ሥምምነት ለምዕራቡ አደጋ ደቅኗል

  • ቪኦኤ ዜና
FILE - In this Nov. 24, 2020, photo, a Long March-5 rocket carrying the Chang'e 5 lunar mission lifts off at the Wenchang Space Launch Center in Wenchang in southern China's Hainan Province.

FILE - In this Nov. 24, 2020, photo, a Long March-5 rocket carrying the Chang'e 5 lunar mission lifts off at the Wenchang Space Launch Center in Wenchang in southern China's Hainan Province.

ቻይናና ሩሲያ የተቀናቃኞቻቸውን ዩናይትድ ስቴትስን የጠፈር ሳተላይት ጂፒኤስ እና የአውሮፓውያኑን ጋሊሊዮ ሳተላይትን የቅኝት ሥርዓት ለመፎካከር የቴክኖሎጂ ጥምረት እየፈጠሩ መሆናቸው ተናገረ፡፡

ይህ የሆነው ሁለቱ ሃገሮች ወታደራዊና ስትራቴጂካዊ ትብብር ለመፍጠር እየተቃረቡ መሆናቸው እየተነገረ ባለበት በዚህ ወቅት መሆኑም ተመልክቷል፡፡

ሁለቱም ሃገሮች ለተጨማሪ እይታ የሚረዳቸውን የሳተላይት ቴክኖሎጂዎች በየሃገሮቻቸው መሬት ላይ ለመትከል ተስማምተዋል፡፡

በዚህ ዓመት መጀመሪያ ላይ የሩሲያን ግሎናስ የተባለውን የሳተላይት ጣቢያ ቻይና በምድሯ እንድትክል ፈቅዳለች፡፡ ሩሲያም በአጸፋው፣ ቻይና ቤይዳው የተሰኘውን የሳተላይት መሳሪያዋን ሩሲያ ውስጥ እንድትተክል ተስማምታለች፡፡

ይሁ ሁለቱ አገሮች ሰፋ ያለውን የዓለም ክፍል እንዲቃኙ ተጨማሪ አቅም የሚፈጥርላቸው መሆኑን ብቻ ሳይሆን በሁለቱ አገሮች መካከል እየታየው ያለው ስምምነት የበለጠ መግባባትን እየፈጠረ መምጣቱን እንደሚያሳይ ተነግሯል፡፡

የአሜሪካ ድምጽ ያነጋገራቸው ባለሙያዎች ሳተላይት የ21ኛው ክፍለ ዘመንን ወታደራዊ አቅም በተለየ መልኩ የሚገነባ መሆኑን ገልጸዋል፡፡

ሁለቱ አገሮች በተለይ ቻይና ከዩናይትድ ስቴት ጋር የምታደርገው ፉክክር ለምዕራቡ ዓለም አደጋ መሆኑንም አስረድተዋል፡፡ የዩናይትድ ስቴትስ የመላከያ ሚኒስትር ሎይድ ኦስተን እኤአ ህዳር 17 ለጋዜጠኞች በሰጡት መግለጫ “ይህን ነገር እጅግ አደገኛ የሚያደርገው በዓለም አቀፉ ማህበረሰብ ላይ የሚደቅነው አደጋ ነው፡፡ ለስትራቴጂካዊ መረጋጋትም አደገኛ ነው” ብለዋል

ባለፈው ሰኔ ለዩናይትድ ስቴትስ ዜና ማሰራጫ ኤንቢሲ ቃለ መጠይቅ የሰጡት የሩሲያው ፕሬዚዳንት ቭላድሚር ፑትን “ከቻይና ጋር ጥልቅ የጠፈር ምርምርን ጨምሮ በሁሉም ዘርፎች እየሠራን ሲሆን ወደፊትም መስራታችንን እንቀጥላለን፡፡ ይህን በማድረግ የሚቃረን ምንም ነገር አላየሁም” ብለዋል፡፡