የቻይናው የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር አስመራ ገቡ

  • ቪኦኤ ዜና

የቻይና የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ዋንግ ዪ እና ኤርትራ ፕሬዚዳንት ኢሳያስ አፈወርቂ

በቻይናው የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ዋንግ ዪ የተመራ የልኡካን ቡድን ኤርትራን ለመጎብኘት በዛሬው ዕለት አስመራ መግባቱና ከፕሬዚዳንት ኢሳያስ አፈወርቂም ጋር ተገናኝቶ መነጋገሩ ተነገረ፡፡

የውጭ ጉዳይ ሚኒስትሩ ዋንግ ዪ ከቻይናው መሪ ፕሬዚዳንት ዢ ጂፒንግ የተላከ መልዕክት ለኤርትራው ፕሬዚዳንት ኢሳያስ አፈወርቂ ማድረሳቸው የተመለከተ ሲሆን ቻይናና ኤርትራ የጋራ ግንኙነታቸውን ለማጠንከር መስማምታቸው ተገልጿል፡፡

የኤርትራው መሪ ቻይናን እንዲጎበኙ ከቻይናው ፕሬዚዳንት ጥሪ የተደረገላቸው መሆኑም ከስፍራው በደረሰን ዘገባ ተመልክቷል፡፡