በአፋር ክልል ከጦርነቱ በኋላ የሕፃናት ጋብቻ በቁጥር እንደጨመረ ተገለጸ

Your browser doesn’t support HTML5

በአፋር ክልል ከጦርነቱ በኋላ የሕፃናት ጋብቻ በቁጥር እንደጨመረ ተገለጸ

በሰሜን ኢትዮጵያ፣ ለሁለት ዓመታት ያኽል የተካሔደው ጦርነት፣ ለሴቶች አስገድዶ መደፈር እና ለተለያዩ ጾታዊ ጥቃቶች ያጋለጠ ነበረ።

ጦርነቱ በፈጠረው ማኅበራዊ ቀውስ፣ በአፋር ክልል የሕፃናት ሴቶች እና የልጃገረዶች ጋብቻ በከፍተኛ ቁጥር እንደጨመረ፣ “በመብቶች እና ዴሞክራሲ እድገት ማዕከል በኢትዮጵያ” (CARD) የተሠራ ጥናት አመላከተ።

የጥናቱን ይዘት እና በክልሉ የሕፃናት ሴቶችን ጋብቻ አስመልክቶ፣ ጥናቱን ያከናወነችው ወጣት የሕግ ባለሞያ ኩልሱማ ኑር እና በአፋር የሴቶች እና ማኅበራዊ ጉዳይ ቢሮ የተ.መ.ድ ቴክኒካል ቡድን ባልደረባ ወሮ. ሰዓዳ መሐመድ፣ ከአሜሪካ ድምፅ ጋራ ቆይታ አድርገዋል።

ዝርዝሩን ከተያያዘው ፋይል ይከታተሉ።