ጨለንቆ ከተማ ላይ የተቃውሞ ስልፍ በማድረግ ላይ የነበሩት አሥራ አምስት ሰዎችን የገደሉ የሠራዊት አባላትና ትዕዛዝ የሰጡ ኃላፊዎች በሕግ እንዲጠየቁ የኦሮምያ ብሄራዊ ክልላዊ መንግሥት አሳሰብ። ግድያው መሣርያ ባልታጠቁ ሰዎች ላይ የተፈፀመ ወንጀል ነው ብለዋል የኦሮምያ ብሄራዊ ክልላዊ መንግሥት ቃል አቀባይ አቶ አዲሱ አረጋ።
አዲስ አበባ —

በሌላም በኩል በወለጋ ዩኒቨርሲቲ ሻምቡ ካምፓስ ብሄርን ለይተው ጥቃት በፈፀሙ፣ ሁለት የትግራይ ተወላጅ ተማሪዎችን በገደሉ አካላት ላይ ሕጋዊ እርምጃ እንደሚወሰድ ቃል አቀባዩ አስታውቀዋል።
በአዲስ አበባ የሚኘው የዩናይትድ ስቴትስ ኤምባሲ ባወጣው መግለጫ ደግሞ በሁለቱም አካባቢዎች ለሞቱት ሰዎች ቤተሰቦች ሀዘኑን ገልጿል።
መንግሥት የዜጎቹን ደኅንነት ማረጋገጡና አጥፊዎቹን ለፍርድ ማቅረቡ አስፈላጊ ነው ብሏል ኤምባሲው።
ለተጨማሪ የተያያዘውን የድምፅ ፋይል ያዳምጡ።
Your browser doesn’t support HTML5