ደቡባዊ የመን ውስጥ የሚካሄደው ውጊያ ወደዋናዋ ወደብ ወደ ሁዲይዳ እየተቃረበ ከሄደ ለብዙ መቶ ሺህ ሕፃናት የሞት ፍርድ ያህል ሊሆን እንደሚችል ሕፃናት አድን ድርጅት አስጠነቀቀ።
ዋሺንግተን ዲሲ —
ደቡባዊ የመን ውስጥ የሚካሄደው ውጊያ ወደዋናዋ ወደብ ወደ ሁዲይዳ እየተቃረበ ከሄደ ለብዙ መቶ ሺህ ሕፃናት የሞት ፍርድ ያህል ሊሆን እንደሚችል ሕፃናት አድን ድርጅት አስጠነቀቀ።
የበጎ አድራጎት ድርጅቱ የሕፃናት አድን የየመን ተጠሪ ታሜር ኪሮሎስ በሰጡት ቃል በዚህ ወሳኝ ወደብ በኩል የሚገባው የምግብ የነዳጅ እናም ሌላም አቅርቦት ብዙ መቶ ሺህ በረሃብ የተጎዱ ሕፃናት በህይወት መቆየት የሚያስችላቸው ምግብ ለማግኘት እንደማይችሉ አስጠንቅቋል።
አሁንም ከአምስት ሚሊዮን በላይ ሕፃናት ረሃብ ለከባድ ቸነፈር ተጋልጠው እንዳሉ ሲታወቅ ሁዲይዳ ወደብ በውጊያው ከተዘጋ ደግሞ የተጎጂዎቹ ሕፃናት ቁጥር በአንድ ሚሊዮን እንደሚጨምር ሕፃናት አድን አስጠንቅቋል።