በጎንደር ሕይወት እየጠፋና ንብረት እየወደመ ነው

  • መለስካቸው አምሃ

ጎንደር /ፎቶ - ፋይል/

በጎንደር ከተማ ከትላንት ጀምሮ በተፈጠረው ውጥረት ሳቢያ ሕይወት እየጠፋና ንብረት እየወደመ መሆኑ ተነገረ።

Your browser doesn’t support HTML5

በጎንደር ሕይወት እየጠፋና ንብረት እየወደመ ነው

በፈደራል የፀጥታ ኃይሎች ተከብበው የነበሩት የወልቃይት ሕዝብ የአማራ ማንነት ጥያቄ ኮሚቴ አባል ዛሬ እጃቸውን ለሰሜን ጎንደር ልዩ ኃይል አዛዥ መስጠታቸው ተገልጿል።

መንግሥት ትናንት ባወጣው መግለጫ "በቁጥጥር ሥር ያዋላቸው የኮሚቴው አባላትና አንዳንድ ቁጥጥር ሥር ያልገቡ አባላት ከአሸባሪዎችና ከፀረ-ሰላም ኃይሎች ጋር ግንኙነት አላቸው" ብሏል፡፡

የኮሚቴው ፀሐፊ ግን ይህን አስተባብለዋል።

የጎንደር ከተ ነዋሪዎች ከተማዪቱ ዛሬም እንዳልተረጋጋች ለአሜሪካ ድምፅ ገልፀዋል። የወልቃይት ሕዝብ የአማራ ማንነት ጥያቄ ኮሚቴ ፀሐፊ አቶ አደራጀው ዋኘው ሁኔታው ከትላንት የባሰ መሆኑን ገልፀዋል።

ዝርዝር ዘገባውን ከተያያዘው የድምፅ ፋይል ያድምጡ።