Your browser doesn’t support HTML5
የቻድ ፕሬዝደንት ኢድሪስ ዴቢ ዕሁድ እለት ከአርባ የሚበልጡ የቻድ ወታደሮችን የገደሉትን በመቶዎች የተቆጠሩ የቦኮ ሐራም ታጣቂዎች ለመደምሰስ ወታደራዊ ዘመቻ አስጀምረዋል፡፡ ቦኮ ሐራም ካሜሩን ፣ናይጄሪያ፣ ኒዠር እና ቻድን በሚያዋስነው በቻድ ሐይቅ ጥቃት አድርሶ ብዛት ያላቸው የቻድ ወታደሮች ገድሏል።
ትላንት አካባቢውን የጎበኙት ዴቢ የተገደሉት ወታደሮች ሥርዓተ ቀብር በማስፈጸም ርዳታ ማድረጋቸውን ጠቅሶ ከካሜሩን ያውንዴ ሞኪ ኤድዊን ኪንድ ያጠናቀረውን ዘገባ ከተያያዘው ፋይል ይከታተሉ።