Your browser doesn’t support HTML5
በማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ጉራጌ ዞን አበሽጌ ወረዳ ከፋኖ ታጣቂ ቡድኖች ጋራ በመገናኘትና ቡድኑን በመደገፍ የተጠረጠሩ ሰዎች፣ ማንነትን በለየ መልኩ ከዐሥር ሰዎች በላይ ከትላንትና ወዲያ መታሰራቸውን የአሜሪካ ድምፅ ያነጋገራቸው ነዋሪዎች ገለጹ።
በዞን የአበሽጌ ወረዳ አስተዳደር ግለሰቦቹ የታሰሩት፣ በማንነታቸው ሳይኾን ከፋኖ ታጣቂ ቡድን ጋራ ግንኙነት በመፍጠር ወንጀል ተጠርጥረው መኾኑን ገልጸዋል።
ነዋሪዎቹ፣ ከሐምሌ 2016 ዓ.ም. ጀምሮ ከ150 በላይ ሰዎች መታሰራቸውን የገለጹ ሲኾን፣ የወረዳው የአስተዳደር የሰላም እና ጸጥታ ጽህፈት ቤት ኃላፊ መቶ አለቃ ፀጋዬ አምድሳ ግን “እኛ ያሰርናቸው 58 ተጠርጣሪዎችን ብቻ ነው። 150 የተባለው ሀሰት ነው” ብለዋል።
ዝርዝሩን ከተያያዘው ዘገባ ይከታተሉ፡፡