መርዝ ያዘለ ደብዳቤ ለትራምፕ በመላክ የተወነጀሉት ካናዳዊት የእስር ቅጣት ተፈረደባቸው

  • ቪኦኤ ዜና
ዋይት ሃውስ ቤተመንግሥት

ዋይት ሃውስ ቤተመንግሥት

አንዲት ካናዳዊት በጊዜው የዩናይትድ ስቴትስ ፕሬዝዳንት ለነበሩት ዶናልድ ትራምፕ ‘ራይሲን’ የተባለ መርዝ በውስጡ ያዘለ እና ዛቻ የሰፈረበት ደብዳቤ ወደ ዋይት ሃውስ በመላካቸው በትላንትናው ዕለት 22 ዓመት የሚጠጋ የእስር ቅጣት ተፈረደባቸው።

የ56 ዓመቷ ፓስካል ፌርዬ

የ56 ዓመቷ ፓስካል ፌርዬ

የ56 ዓመቷ ፓስካል ፌርዬ ለትራምፕ እና ቴክሳስ ክፍለ ግዛት ውስጥ ለሚገኙ የፖሊስ ባለስልጣናት በላኳቸው ደብዳቤዎች የባዮሎጂያዊ የጦር መሳሪያ ክልከላ ህጎችን በመተላለፍ ጥፋተኛ መሆናቸውን አምነው ቃላቸውን ሰጥተዋል።

ተከላካይ ጠበቃቸው ዩጂን ኦም በትላንትናው ዕለት በሰጡት አስተያየት፡ ፌርዬ ከፈረንሳይ የመጡ ስደተኛ መሆናቸውን፣ የከፍተኛ ትምሕርት ተከታትለው በምሕንድስና የሁለተኛ ድግሪ ማግኘታቸውን እና እንዲሁም ሁለት ልጆች ያለ አባት የሚያሳድጉ እናት መሆናቸውን ጨምረው ተናግረዋል።

በ262 ወራት እስራት እንዲቀጡ የፈረዱባቸው የዩናይትድ ስቴትሱ የከፍተኛ ፍርድ ቤት ዳኛ ዳቢኒ ፍሪድሪክ፡ በፌርዬ የቅጣት ማቅለያ ስምምነት ላይ በሰፈረው መሰረት ከእስር እንደተለቀቁም ከአገር እንዲወጡ የሚጠይቅ ቅጣት ጨምረው በይነዋል።