የካሜሩን መንግሥት ለኮቪድ-19 የተዋጣ ገንዘብ አያያዝ ላይ ምርመራ እንዲደረግ ተጠየቀ

  • ቪኦኤ ዜና
ፎቶ ፋይል

ፎቶ ፋይል

የካሜሩን መንግሥት ሲቪሉ ህዝብ ለኮቪድ-19 ጉዳይ ያዋጣውን ገንዘብ አያያዝ ላይ፣ ምርመራ እንዲደርግ ማዘዙ ታወቀ። መንግሥት ትዕዛዙን ያስተላለፈው፣ የመብት ቡድኖች ባደረጉት ጫና ነው ተብሏል።

ለመብት የቆሙት ቡድኖች እንደሚሉት፣ በገንዘብና በቁስ ከተዋጣው $40 ሚሊዮን ዶላር አብዛኛው ተጭበርብሯል። ለኮቪድ-19 ተጋላጮች የተለገሰ 4,000 ኩንታል ሩዝ፣ ህገ-ወጥ በሆነ መንገድ መሽጡን፣ የመብት ቡድኖቹ ከተናገሩ በኋላ፣ ከፍተኛ ቁጣ መቀስቀሱ ተገልጿል።