በዐማራ ክልል ላይ የተጣለው የአስቸኳይ ጊዜ ዐዋጅ ሰላምን ለማምጣት ባለመቻሉ እንዲነሣ ተጠየቀ

Your browser doesn’t support HTML5

በዐማራ ክልል ላይ የተጣለው የአስቸኳይ ጊዜ ዐዋጅ ሰላምን ለማምጣት ባለመቻሉ እንዲነሣ ተጠየቀ

የሚኒስትሮች ምክር ቤት በዐማራ ክልል አጋጥሟል ያለውን የጸጥታ መደፍረስ፣ በመደበኛው የሕግ ሥነ ሥርዐት ለመቆጣጠር የማይቻል ነው፤ በሚል፣ የአስቸኳይ ጊዜ ዐዋጅ ከደነገገ ሦስት ወራት አልፈውታል፡፡

የዐማራ ብሔራዊ ንቅናቄ(አብን) ፓርቲ አባል እና የምክር ቤት ተመራጭ አቶ አበባው ደሳለው፣ መንግሥት፣ በአስቸኳይ ጊዜ ዐዋጅ የሕዝቡን ጥያቄ መመለስ እንደማይችል ተረድቶ እንዲነሣ ሊያደርግ ይገባል፤ ይላሉ፡፡

የእናት ፓርቲ ፕሬዚዳንት ዶክተር ሰይፈ ሥላሴ አያሌው በበኩላቸው፣ በሰሜኑ የአገሪቱ ክፍል አጋጥሞ ከነበረው ጦርነት ትምህርት መውሰድ ባለመቻሉ ምክንያት፣ ያለፉት ሦስት ወራት ንጹሐን ዜጎች ለሥቃይ የተዳረጉበት እንደኾነ ይገልጻሉ፡፡

መንግሥት በበኩሉ፣ አብዛኛው የዐማራ ክልል አካባቢዎች ወደ ሰላማዊ ኹኔታ እንደተመለሱ፣ በቅርቡ በሰጠው መግለጫ አስታውቋል፡፡

ዝርዝሩን ከተያያዘው ፋይል ይከታተሉ።