ጠቅላይ ሚኒስትር አብይ አሕመድ ሥልጣን ከተረቡ ማግሥት አንስቶ ሀገሪቱን ሰቅዞ ይዟት የቆየውን ውጥረት ለማርገብ ይመስላል ወደተለያዩ አካባቢዎች እየተጓዙ ሕዝቡን በቀጥታ እያነጋገሩ ናቸው።
ዋሺንግተን ዲሲ —
ጠቅላይ ሚኒስትር አብይ አሕመድ ሥልጣን ከተረቡ ማግሥት አንስቶ ሀገሪቱን ሰቅዞ ይዟት የቆየውን ውጥረት ለማርገብ ይመስላል ወደተለያዩ አካባቢዎች እየተጓዙ ሕዝቡን በቀጥታ እያነጋገሩ ናቸው።
ሕዝቡም “አንገብጋቢ” የሚላቸውን ጥያቄዎቹን “ይፈታሉ” በሚል ተስፋ እያቀረበላቸው ነው። እርሳቸውም ሀገሪቱ ከፍተኛ ችግሮች እንዳሏት ከማመን አልፈው “አግዙኝና ተባብረን” እያሉ ናቸው።
ባለፈው ሣምንት ማብቂያ ላይም ተመሣሣይ በሆነ መንፈስ የሀገሪቱን የግል ባለኃብቶች በአዲስ አበባ ሸራተን ሆቴል ሰብስበው ማነጋገራቸው ይታወሳል።
በዚያ መድረክ ላይ አንኳር አንኳር የተባሉ የሃገሪቱ የምጣኔ ኃብት ዕድገት ማነቆ የተባሉ ዕክሎች ከንግድና መዋዕለ ነዋይ ማኅበረሰቡ ለጠቅላይ ሚኒስትሩ ቀርበዋል፤ የብሔራዊ ባንክ መመሪያና ፖሊሲ፣ የውጭ ምንዛሪ እጥረት፣ ኮንትሮባንድ፣ ሙስና፣ አለመረጋጋት ወይም የሰላም ችግርና ሌሎችም ተጠቅሰዋል።
ጠቅላይ ሚኒስትሩ “ዐብይ” ለተባሉ ለአንድ ሁለቱ የሃገሪቱ ችግሮች የሰጡትን መልስ እንዲገመግሙ የምጣኔ ኃብት ምሁራንን ጋብዘናል። ችግሮቹን “ለዘለቄታው ያስወግዳሉ” የሚሏቸውን ሃሣቦች እንዲጠቁሙ ጠይቀናቸዋል።
የተያያዘውን የድምፅ ፋይል ያዳምጡ።
Your browser doesn’t support HTML5
Your browser doesn’t support HTML5