የአዲሱ ጠቅላይ ሚኒስትር ፈተናዎች - ለጥያቄዎ መልስ

ጠቅላይ ሚኒስትር ዶ/ር አብይ አህመድ

አዲሱ ጠቅላይ ሚኒስትር ሃገሪቱን ለማረጋጋት መጀመሪያ መውሰድ ያለባቸው እርምጃዎች የአስቸኳይ ጊዜ አዋጁን ማንሳት እንደሆነ ብዙዎች ይመክራሉ።

አዲሱ ጠቅላይ ሚኒስትር ሃገሪቱን ለማረጋጋት መጀመሪያ መውሰድ ያለባቸው እርምጃዎች የአስቸኳይ ጊዜ አዋጁን ማንሳት እንደሆነ ብዙዎች ይመክራሉ።

ዓለምአቀፍ የሰብዓዊ መብቶች ተሟጋቾች፣ የኢትዮጵያ የፖለቲካ ተዋናዮች፣ ዲፕሎማቶችም ጭምር አዋጁ እንዲነሣ ድምፃቸውን አሰምተዋል።

በጠቅላይ ሚኒስትሩ ፈተናዎች ላይ የጥያቄዎ መልስ ዝግጅት የጋበዛቸው ሁለት ምሁራን ስለአስቸኳይ ጊዜ አዋጁ አስፈላጊነትና አተገባበር ምልስ ሰጥተዋል፤ ሌሎችም የጠቅላይ ሚኒስትሩ ፈታኝ ሁኔታዎች ተነስተዋል።

ለአድማጮች ጥያቄዎች መልስ የሰጡት በወታደራዊው አስተዳደር ዘመን የኢትዮጵያ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር፣ የእርዳታ ማስተባበሪያና ማቋቋሚያ ኮሚሽነር፣ ቀደም ሲልም የኤርትራ ክፍለሃገር አስተዳዳሪ የነበሩት የሕግ ምሁሩ ሻለቃ ዳዊት ወልደጊዮርጊስ፣ እንዲሁም በአኵስም ዩኒቨርሲቲ የፖለቲካ ሣይንስና የዓለምአቀፍ ግንኙነቶች መምህሩ አቶ ገብረመድኅን መዝገበ ናቸው።

ለሙሉው ዝግጅት የተያያዘውን የድምፅ ፋይል ያዳምጡ።

Your browser doesn’t support HTML5

የአዲሱ ጠቅላይ ሚኒስትር ፈተናዎች - ለጥያቄዎ መልስ (ክፍል አንድ)

Your browser doesn’t support HTML5

የአዲሱ ጠቅላይ ሚኒስትር ፈተናዎች - ለጥያቄዎ መልስ (ክፍል ሁለት)