የኦባማ ጉብኝት በኢትዮጵያ - ለጥያቄዎ መልስ ጥያቄዎችዎን ይላኩ

U.S. President Barack Obama speaks on the phone with Saudi Arabia's King Abdullah from the Oval Office of the White House in Washington September 10, 2014. President Barack Obama called Saudi Arabia's King Abdullah on Wednesday ahead of an evening speech

የፕሬዚዳንት ባራክ ኦባማ የኢትዮጵያ ጉብኝት

የዩናይትድ ስቴትስ ፕሬዚደንት ባራክ ኦባማ የፊታችን ነኀሴ 19 እና 20 ኢትዮጵያን ሊጎበኙ ነው። በጉብኝታቸው ወቅት ከአገሪቱ መሪዎች ጋር ስለ ጋራ ጉዳዮች ይወያያሉ፥ ከአፍሪቃ ኅብረት መሪዎችም ጋር ይገናኛሉ።

የኢትዮጵያ መንግሥት ተቃዋሚዎች “ገዥው ኢህአዴግ ሰብአዊ መብቶችን ይረግጣል፥ ጋዜጠኞችን ያስራል፣ ተቃናቃኝ ፓርቲዎችን ያፍናል፣ ምርጫ አጭበርብሯል …” በማለት የፕሬዚዳንቱን ወደ ኢትዮጵያ መሄድ ይቃወማሉ፡፡

ዩናይትድ ስቴትስ ከኢትዮጵያ ጋር በአካባቢ ፀጥታ፣ በልማት እና በንግድ የፖሊሲ ግንኙነት እንዳላት ይታወቃል፡፡ ከእነዚህ ጭብጦች አንፃር የፕሬዚዳንቱን ጉዞ አስመልክቶ የሚተነትኑና መልስ የሚሰጡ ሁለት ምሁራንን ለጥያቄዎ መልስ ዝግጅት ጋብዘናል።

ከፕሬዚደንቱ የኢትዮጵያ ጉዞ ጋር በተያያዘ ለጥያቄዎቻችሁ መልስና ማብራሪያ የሚሰጡት ፕሮፌሰር ዓለማየሁ ገብረማሪያም በካሊፎርኒያ ስቴት ዩኒቨርሲቲ የፖለቲካ ሣይንስና የሕግ ፕሮፌሰር፣ እንዲሁም ዶክተር መሃሪ ታደለ ማሩ የምሥራቅ አፍሪቃ አገሮች የጋራ ልማት ባለሥልጣን - ኢጋድ በአፍሪቃ ኅብረት የፀጥታ ጉዳዮች ተንታኝ ናቸው፡፡

ጥያቄዎችዎን በ202-205-9942 በውስጥ መሥመር 14፤ እንዲሁም በኢሜል Horn@voanews.com ብለው አሁኑኑ አድርሱን፡፡