በቅድሚያ ጥያቄዎቻችሁን ያደረሣችሁን የፕሮግራማችን ተሣታፊዎችና መልስ ለሰጡልን ምሁራን ምሥጋና እናቀርባለን። የዛሬው የ“ለጥያቄዎ መልስ” ርዕሰ ጉዳይ ሕገወጥ የመሬት ይዞታና በተያዙ ቦታዎች ላይ የተሠሩ ቤቶችን ማፍረስ እያስከተለ ስላለው ማኅበራዊ ቀውስ ነው።
ዋሺንግተን ዲሲ —
ቤቶቹን አፍራሽ ባለሥልጣናት “ሕገወጥ የመሬት ይዞታን የሚከለክል አዋጅ እያስከበርን ነን” ቢሉም በሚሊዮኖች የሚቆጠሩ በእርስ በርስ ግጭቶች ተፈናቅለው ጊዜያዊ መጠለያ ውስጥ በሚገኙበት ሃገር ሕዝብን የሚያፈናቅሉ ተጨማሪ እርምጃዎችን በጥብቅ የሚኮንኑ ብዙ ናቸው። ይህ ቤተሰቦችን ያለመጠለያ ማስቀረት ከሚፈጥረው የሥነ-ልቦናና ኢኮኖሚያዊ ቀውስ በተጨማሪ መሆኑ ነው።
በተለይ ደግሞ ሕገወጥ የመሬት ሽያጩንም ያከናወኑት ከደላላዎች ጋር የሚመሣጠሩ ባለሥልጣናት መሆናቸው እየተነገረ ነው።
በኢትዮጵያ በትልቅነቷ ከአዲስ አበባ ቀጥሎ ሁለተኛ የሆነችው የድሬዳዋ የመሬት ልማትና አስተዳደር ቢሮ ኃላፊ ዶ/ር ደራራ ሁቃ አስተዳደራቸው ቤቶችን ከማፍረስ ይልቅ የተለየ እርምጃ መውሰዱን ያስረዳሉ።
ኢትዮጵያ ውስጥ ለሚነሱ የ‘ይገባኛል’ ጥያቄዎች፣ ለአብዛኞቹ ሕገመንግሥቱን ተጠያቂ የሚያደርጉ አሉ። የኢትዮጵያን ሕገመንግሥት የመረመሩ የሕግ ምሁርና ጠበቃ ደረጀ ደምሴን ከቦስተን - ማሳቹሴትስ ይዘናል።
ለተጨማሪ ዘገባ የተያያዘውን የድምፅ ፋይል ያዳምጡ።
Your browser doesn’t support HTML5