ካሊፎርኒያ የሎሳንጀለስ ከተማን ሰሜን ምዕራብ አካባቢ ያደረሰው ሰደድ እሳት

  • ቪኦኤ ዜና
ምዕራባዊ ዩናይትድ ስቴትስዋ ክፍለ ሀገር ካሊፎርኒያ የሎሳንጀለስ ከተማን ሰሜን ምዕራብ አካባቢ ያደረሰውን ሰደድ እሳት ለመቆጣጠር የእሳት አደጋ ሰራተኞች ጥረታቸውን ቀጥለዋል፡፡ ቃጠሎው በስፋቱና ባደረሰው ውድመት በክፍለ ሀገርዋ ታሪክ ከደረሱት ከባድ ቃጠሎዎች አንዱ መሆኑ ከወዲሁ እየተነገረ ነው፡፡

ምዕራባዊ ዩናይትድ ስቴትስዋ ክፍለ ሀገር ካሊፎርኒያ የሎሳንጀለስ ከተማን ሰሜን ምዕራብ አካባቢ ያደረሰውን ሰደድ እሳት ለመቆጣጠር የእሳት አደጋ ሰራተኞች ጥረታቸውን ቀጥለዋል፡፡ ቃጠሎው በስፋቱና ባደረሰው ውድመት በክፍለ ሀገርዋ ታሪክ ከደረሱት ከባድ ቃጠሎዎች አንዱ መሆኑ ከወዲሁ እየተነገረ ነው፡፡

ከአንድ ሳምንት በፊት የጀመረው ሰደድ እሳቱ እስካሁን ዘጠኝ መቶ ሠላሳ ካሬ ኪሎ ሜትር ስፋት ያለው አካባቢ አውድሟል፡፡ ሳንታ ባርባራ ወረዳ ውስጥ ስምንት መቶ ሕንፃዎችን አጋይቷል፡፡

እስካሁን በቁጥጥር ሥር ያዋልነው አሥር ከመቶውን ብቻ ነው ያሉት ባለሥልጣናቱ በኃይለኛው ንፋስ ታግዞ ያለው አካባቢ ማዳረሱ እንደሚቀጥል ሰግተዋል፡፡