የምዕራብ ዩናይትድ ስቴትስዋ ካሊፎርኒያ ክፍለ ግዛት የተዛመተው የደን ሰደድ እሳት ዛሬም ቀጥሏል
አገረ ገዥው ጋቪን ኒውሰም ቃጠሎውን ለመቆጣጠር ዓለም አቀፍ እገዛ ተማጽነዋል
ወደ አምስት መቶ ስድሳ በሚጠጉ ስፍራዎች በክፍለ ግዛቱዋ ዙሪያ የተቀሰቀሰውን ቃጠሎ ለማጥፋት አስራ ሁለት ሺህ የእሳት አደጋ ሰራተኞች እይተረባረቡ ናቸው
በሰደድ እሳቱ እስካሁን ቢያንስ አምስት ሰዎች የሞቱ ሲሆን የእሳት አደጋ ሰራተኞችን ጨምሮ አርባ ሶስት ሰዎች ተጎድተዋል፥ ያሁኑ የአየር ሁኒታ ቃጠሎውን ያባብሰዋል የሚል ስጋት አለ
ፕሬዚደንት ዶናልድ ትረምፕ አድርጉ ያልኩዋቸውን ስላልሰሙ ነው ብለው ለቃጠሎው የክፍለ ግዛትዋ አስተዳዳሪዎች ወቅሰዋል
ጫካው ውስጥ ለዓመታት የተከመረውን ቅጠሉን እና የወደቀ ዛፍ ጥረጉ ብያቸው ነበር ብለዋል