ምርታቸውን በከፍተኛ ዋጋ የሸጡ የቡና ገበሬዎች

Your browser doesn’t support HTML5

ምርታቸውን በከፍተኛ ዋጋ የሸጡ የቡና ገበሬዎች

ቡናቸውን በቀጥታ ለዓለም አቀፍ ገበያ ያቀረቡ የሲዳማ አርሶ አደሮች የቡና ምርታቸውን በከፍተኛ ዋጋ መሸጣቸውን ለአሜሪካ ድምፅ ተናገሩ።

በዓለም አቀፍ ደረጃ የልዩ ጣዕም ቡና ባለቤቶችን በየዓመቱ እያወዳደረ የሚሸልመው ካፕ ኦፍ ኤክሰሌንሲ (COE) የተባለ ዓለም አቀፍ ድርጀት የኢትዮጵያ ፕሮጀከት ማናጀር አቶ እንዳለ አስፋው ከኢትዮጵያ የ600 አርሶ አደሮች ቡና ተወዳድሮ የ40ዎቹ ቡና አሸናፊ መኾኑን አረጋግጠዋል።

የኢትዮጵያ ቡናና ሻይ ባለሥልጣን ዋና ዲሬክተር ዶ.ር አዱኛ ደበላ የኢትዮጵያ ቡና በዓለም በከፍተኛ ዋጋ መሸጡን ተናግረዋል።

የCOE ዕውቅና መርኃ ግብር የአርሶ አደሮች በጥራት እንዲያመርቱ አነሳስቷቸዋል ሲሉ ተናግረዋል።