ቡሩንዲ ውስጥ በእሥር ላይ የነበሩ ጋዜጠኞች ተለቀቁ

  • ቪኦኤ ዜና

ቡሩንዲ ውስጥ የመብት ቡድኖች መሰረተ ቢስ ባሉት ክስ ተፈርዶባቸው ለአንድ ዓመት በእስር ላይ የነበሩት አራት ጋዜጠኞች በፕሬዚዳንታዊ ምህረት ተለቀቁ።

የመጨረሻው በሀገሪቱ የሚንቀሳቀስ ነጻ የመገናኛ ብዙሃን አውታር የሆነው ድርጅት አባላት የነበሩት ጋዜጠኞች የታሰሩት ከኮንጎ ዲሞክራሲያዊ ሪፖብሊክ በድንበር ሰርጎ የገባ ታጣቂ እንቅስቃሴ ላይ ለመዘገብ ድንበሩ አካባቢ በተገኙበት እንደነበር ተገልጿል።

የሃገር ጸጥታ በማደፍረስ ተግባር ፈጽመዋል ተብለው ሁለት ዓመት ተኩል እስራት ተፈርዶባቸው ነው የታሰሩት።