ቡርጂ ውስጥ ግጭት ምክኒያት ዘጠኝ ሰዎች መገደላቸውን የአካባቢው አስተዳዳሪዎች ገለፁ

Your browser doesn’t support HTML5

ቡርጂ ውስጥ ግጭት ምክኒያት ዘጠኝ ሰዎች መገደላቸውን የአካባቢው አስተዳዳሪዎች ገለፁ

ቡርጂ ወረዳ ሶየመ ከተማ ውስጥ በተፈፀመ ጥቃት ዘጠኝ ሰዎች መገደላቸውን እና ሌሎች 20 ሰዎች ደግሞ ከባድ እና ቀላል ጉዳት እንደደረሰባቸው የአካባቢው አስተዳዳሪዎች ገለፁ።

ቅዳሜ ግንቦት 27/2014 ዓ.ም አካባቢውን ከሚያጎራብቱ የኦሮሚያ ክልል ከተሞች እና ከሌሎች የደቡብ ክልል ዞኖች እና ወረዳዎች ቡርጂ ልዩ ወረዳ ሶየመ ከተማ ውስጥ ለገበያ የተሰበሰቡ ሰዎች ላይ ጥቃት መከፈቱን አስተዳዳሪዎቹ ጨምረው ተናግረዋል።

ዘገባው የገልሞ ዳዊት ነው።