በኦሮሚያ ክልል ቡራዩ ከተማ ውስጥ እስር ላይ የሚገኙ የኦሮሞ ነፃነት ግንባር አመራር አባላት የት እንዳሉ እንደማያውቁ ጠበቃቸው ለአሜሪካ ድምፅ ተናግረዋል።
እሥረኞቹ ከትናንት በስተያ ማክሰኞ ከእስር ቤት በኦሮሚያ ፖሊስ ኮሚሽን መወሰዳቸውን ጠበቃቸው ቢናገሩም ያሉበትን ሁኔታና ቦታ ከቡራዩ ፖሊስ መምሪያ፣ ከኦሮሚያ ፖሊስ ኮሚሽን፣ ከኦሮምያና ፌዴራል ጠቅላይ አቃቤ ለማወቅ ቪኦኤ ያደረጋቸው ጥረቶች አልተሳኩም።
የኦሮሞ ነፃነት ግንባር ሁኔታው እንዳሳሰበው አስታውቋል።
ሙሉ ዘገባውን ከተያያዘው ፋይል ይከታተሉ።