ዋሽንግተን —
“ይሄ የሕዝቡ ድል ነው። መልካም ዜጎች ያስመዘገቡት ድል ነው። ይሄ በግዙፉ ባንኮችና የንግድ ድርጅቶች እና ፖለቲካ በሚያሳድረው ጫና ላይ የተገኘ ድል ነው። የተደቀኑትን አያሌ ፈተናዎች አልፎ ትክክለኛ ነገር እውን የሆነበት።”ናይጅል ፋርጅ የቀኝ ዘመሙ ኢንዲፐንደንት ፓርቲ መሪ
እንግሊዛውያን በትላንቱ ሕዝበ ውሳኔ አገራቸው ከአውሮፓ ሕብረት እንድትወጣ መረጡ። ውሳኔውን ተከትሎም በዓለም ዙሪያ የሚገኙ የተለያዩ አገሮች የገንዘብና የአክስዮን ገበያዎች ከዳር እስከዳር ክፉኛ መዋዠቅ ሲያሳዩ ውለዋል።
የዚህ ውሳኔን የዛሬ፥ የነገና እንዲሁም ዘላቂ አንድምታዎች የዳሰሰ ትንተና ከዚህ ያድምጡ፤
Your browser doesn’t support HTML5
የብሪታንያ ከአውሮፓ ሕብረት መውጣትና ውሳኔው የደቀናቸው ሥጋቶች
“የብሪታንያ ሕዝብ በተለየ አቅጣጫ ለመጓዝ ግልጽ ውሳኔ አድርጓል። በመሆኑም አገሪቱ ወደዚያ ሌላ አቅጣጫ የሚመራት አዲስ መሪ ያስፈልጋታል።”የእንግሊዙ ጠቅላይ ሚንስትር ዴቪድ ካሜሮንYour browser doesn’t support HTML5
የእንግሊዙ ጠቅላይ ሚንስትር ዴቪድ ካሜሮን በመጪው ወራት ከሥልጣን እንደሚለቁ ያስታወቁበት መግለጫ