ለኮሮና ቫይረስ የተጋለጠ ሰው ቫይረሱን ለሌላ ሰው ለማስተላለፍ በሚችልበት ደረጃ ላይ ይሁን አይሁን ምራቁን በቀላሉ በመመርመር ለማወቅ የሚያስችል ዘዴ መፍጠሩን አንድ የብሪታንያ ኩባኒያ አስታወቀ።
ቫቲክ የተባለው ኩባኒያይህ የምርመራ መንገድ እጅግ በጣም ትክክለኛ ውጤት የሚያሳይመሆኑን እናከተፈተሸባቸው ሰዎች ውስጥ በአንዳቸውም ላይ የተሳሳተ የምርመራ ውጤት እንዳላሳየ ገልጿል።
ይህ የሰዎችን የዕለት ከዕለት ኑሮ ወደተለመደው ለመመለስ እጅግ የሚጠቅም ግኝት ነው ያለው ኩባኒያውእዚህ የምርመራ ዘዴ ላይ የሰራንበት ዋናው ምክንያት ሰዎች በሳምንት ውስጥ በተደጋጋሚ ቢመረመሩበትየማይከብድ ወይም የሚያስከፋ ባለመሆኑ ነው ሲል ተናግሯል።
የምርመራው ውጤት በአስራ አምስት ደቂቃ የሚደርስ መሆኑን ነው ኩባኒያው ያስታወቀው።
ይህ በምራቅ የኮሮና ቫይረስ መመርመሪያ እስካሁን ለህዝብ አገልግሎት እንዳልቀረበ እና ተጨማሪ ፍተ ላይ መሆኑን የገለጸው ኩባኒያው በቀጥታ ለተጠቃሚው ለማቅረብ ፈቃድ እንዲሰጠን ማመልከቻ እናስገባለን ብሏል።
ይህ በዚህ እንዳለ ህብረተሰቦችን፥ ኢኮኖሚዎች እና መንግሥታትን ያናጋው የኮቪድ አስራ ዘጠኝ ዐለም አቀፍ ወረርሽኝ ዐለም እቀፍ የጤና ደህንነት ሳይኖር ዐለም አቀፍ ጸጥታ እንደማይኖር አሳይቶናል ሲሉ የዐለም የጤና ድርጅት ዋና ስራ አስኪያጅ ዶክተር ቴድሮስ አድሃኖም ተናገሩ።
ዶክተር ቴድሮስ ይህን የተናገሩት በቅርቡ ለአውሮፓ ህብረት የፖለቲካ እና የጸጥታ ኮሚቴ አምባሳደሮች እና ተወካዮች ባደረጉት ንግግር ነው።
ይህን ወረርሺኝ ለማክተም ከማናቸውም ሁነኛ የሆነው መንገድ በክትባቱ አቅርቦት እና ተደራሽነት ጉዳይ ዕውነተኛ ዐለም አቀፍ ትብብር ማድረግ ነው ብለዋል።
"የክትባቱ ክፍፍል መዛባቱን በቀጠለ መጠን ማህበራዊ እና ኢኮኖሚያዊ አለመረጋጋቱ ይራዘማል፥ ያ ሲሆን ቫይረሱ ለመዛመት እና ራሱን ለመቀያየር ያመቸዋል" ያሉት ዶክተር ቴድሮስ አድሃኖም "ከተቀረው ዐለም ተለይቶ የራሱን ህዝብ ብቻ በመክተብ ከወረርሽኙ ለመገላገል የሚችል ሃገር እንደሌለ ሁሉም ሊገነዘበው ይገባል" ብለዋል።
በሌላ የኮቪድ አስራ ዘጠኝ ዜና ኮቪድ አስራ ዘጠኝ እ አ አ ባለፈው 2020 ዐመተ ምህረት ያለማቋረጥ ከፍ እያለ የነበረውን አማካዩን የሰዎች በህይወት መቆያ ዕድሜ በድንገት ባለበት እንዲቆም አድርጎታል ሲል ዘ ኢኮኖሚስት መጽሄት ላይ የወጣው ሪፖርት አመለከተ።
ኢኮኖሚስት ባወጣው ሪፖርት እንዳለው ባለፉት 2019 እና 2020 ዐመተ ምህረት መካከል የሰዎች ዕድሜ አማካይ ተጠባቂ ርዝማኔ ቅኝት ከተደረገባቸው ሃያ ስምንት ሀገሮች መካከል ከሁለቱ በስተቀር በሁሉም ቀንሷል።
ዴንማርክ እና ኖርዌይ እንዲሁም ፊንላንድ ውስጥ አማካዩ የዕድሜ ምጣኔ ከፍ ማለቱን ነው ሪፖርቱ ያመለከተው።
በዩናይትድ ስቴትስ ጣሊያን ፖላንድ እና ስፔይን የወንዶች ዕድሜ አመካይ ከአንድ ዐመት በሚበልጥ መቀነሱን ሪፖርቱ ጠቁሟል።
ዘ ኢኮኖሚስት ባወጣው ሌላ ሪፖርት ደግሞ ዩናይትድ ስቴትስ ውስጥ በኮቪድ አስራ ዘጠኝ ምክንያት የሚሞቱት ሰዎች ቁጥር ከሌሎቹ ሃብታም ሃገሮች በስምንት ዕጥፍ ያህል የሚበልጥ መሆኑን አመለከተ።
ይህ የሆነው የኮቪድ ክትባት መከተብ ላይ ያለው ማመንታት እና ሌሎችም ምክንያቶች የተነሳ መሆኑን ነው ሪፖርቱ ያስረዳው።
አሚሪካ ውስጥ " ክትባቱን በተመለከተ በተለይም በሪፐብሊካኖች ዘንድ ያለው ተቃውሞ እና እምቢተኝነት የሚያሳስብ ነው " ብሏል።