ብሪታንያ ሩሲያን አስጠነቀቀች

  • ቪኦኤ ዜና

የብሪታንያ ጠቅላይ ሚኒስትር ቴሬሳ ሜይ እና የሩስያው ፕሬዚዳንት ቭላዲሚር ፑቲን

ሩስያና የብሪታንያ ግንኙነት ጤናማ ሆኖ እንዲቀጥል ከተፈለገ፣ ሩስያ ኃላፊነት የጎደለው የማፈራረስ ተግባሯን ማቆም አለባት ሲሉ፣ የብሪታንያ ጠቅላይ ሚኒስትር ቴሬሳ ሜይ ለሩስያው ፕሬዚዳንት ቭላዲሚር ፑቲን አስጠነቀቁ።

ባለፈው ዓመት ሶልስበሪ ውስጥ በሰርጌ ስክሪፓል ላይ ለደረሰው ጥቃት ተጠያቂዎች የሆኑት ሁለቱ ሩስያውያን ለፍርድ መቅረብ እንዳለባቸው፣ ቴሬሳ ሜይ ለሩስያው መሪ እንዳሳሰቡ፣ ዛሬ ዐርብ ከቢሯቸው ይፋ የሆነው መግለጫ አመልክቷል።

የጠቅላይ ሚኒስትር ሜይ አስተያየት የተሰማው፣ ኦሳካ ጃፓን በሚካሄደው፣ የጂ20 ጉባዔ ጎን ከፕሬዚደንት ፑቲን ጋር በተገናኙበት ወቅት ነው።