እንግሊዝን ከአውሮፓ ኅብረት አባልነት ያላቅቃል የተባለው ስምምነት

  • ቪኦኤ ዜና
ጠቅላይ ሚነስትሯ ቴሬሳ ሜይ

ጠቅላይ ሚነስትሯ ቴሬሳ ሜይ

እንግሊዝን ከአውሮፓ ኅብረት አባልነት ያላቅቃል የተባለውን ስምምነት የፓርላማው የሕግ መምሪያ እንዲያፀድቅላቸው ለማቅረብ አስበውት የነበረውን ረቂቅ ጠቅላይ ሚነስትሯ ቴሬሳ ሜይ ዛሬ ሳያቀርቡ ቀሩ።

እንግሊዝን ከአውሮፓ ኅብረት አባልነት ያላቅቃል የተባለውን ስምምነት የፓርላማው የሕግ መምሪያ እንዲያፀድቅላቸው ለማቅረብ አስበውት የነበረውን ረቂቅ ጠቅላይ ሚነስትሯ ቴሬሳ ሜይ ዛሬ ሳያቀርቡ ቀሩ።

ጠቅላይ ሚኒስትሯ ከኅብረቱ ላይ ለሁለት ሣምንታት ያህል ብራስልስ ላይ የሠሩትን የስምምነት ሰነድ የድምፅ ቀን ማሸጋገራቸው እንዲሁም የተመሳቀለውን ፍቺ ይበልጥ አመሳቅሎታል ሲሉ ታዛቢዎች ተናግረዋል።

የሕግ መምሪያው እንደራሴዎች ለአራት ቀናት ያደረጉት አተካራ የበዛበት ክርክርና የእግሊዝና የአውሮፓ ኅብረት ፍቺ ጉዳይ የሚገኝበት ሁኔታ በእንግሊዛዊያን ዘንድም እጅ እጅ የሚል ጠረን እየበረታበት በመጣበት ወቅት የሜይ ከፓርላማው ሕንፃ ያለስኬት መውጣት ምናልባት የመንግሥታቸውን ፍፅሜም ሳያጭር እንደማይቀር ተተንብይዋል።