ሞስኮ ውስጥ አንድ የፖሊስ ዓባል ላይ ባለፈው ሰኞ ጥቃት ሰንዝሯል የተባለ አሜሪካዊ ፖሊስ በቁጥጥር ሥር መዋሉን መርማሪዎች ዛሬ ረቡዕ አስታውቀዋል።
ስሙ ያልተገለጸው አሜሪካዊ ሰኞ ዕለት ወደ ፖሊስ ጣቢያ መወሰዱን፣ በዛም ሳለ መታወቂያ እንዲያሳይ ሲጠየቅ በፖሊስ ዓባል ላይ ጥቃት መሠንዘሩን ‘የሩሲያ የምርመራ ኮሚቴ’ የተሰኘ አካል አስታውቋል።
ግለሰቡ ያልተገባ ባሕሪ በማሳየቱ ወደ ፖሊስ ጣቢያ መወሰዱን ፖሊስ አመልክቷል።
የግለሰቡ መያዝ ዜና የመጣው በቅርቡ አሜሪካና ሩስያ ባደረጉት የእስረኞች ልውውጥ ጋዜጠኞችንና ወታሮችን ጨምሮ 16 የሚሆኑ አሜሪካውያን መለቀቃቸውን ተከትሎ ነው።
በሩሲያ በርካታ የአሜሪካና የምዕራብ ሃገራት ዜጎች በእስር ላይ ይገኛሉ።
ስሙ ያልተገለጸው አሜሪካዊ በፍርድ ቤት ጥፋተኛ ከተባለ በሩሲያ ሕግ መሠረት በአምስት ዓመት እስር ሊቀጣ እንደሚችል ታውቋል።