የአውሮፓው ህብረት ዋና ተደራዳሪ ማይክል ባርኒየር ብሪታንያ ከህብረቱ የምትወጣበት ሥምምነት ሳይደረግ ፍቹ ሊፈፀም ወደ ሚችልበት ሁኔታ እየተጠጋች ነው ብለዋል።
ዋሺንግተን ዲሲ —
ባርኔየር ብራሰልስ ሆነው ባደረጉት ንግግር አሁንም ቢሆን ብሪታንያ ካለ ምንም ሥምምነት መውጣቱን ለማስወገድ የምትችልበት ተስፋ አለ ብለዋል። ይሁንና ብሪታንያ ያሏት አማራጮች ውሱን መሆናቸውን ገልፀዋል። የብሪታንያ ምክር ቤት ቴሬሳ ሜይ ከአውሮፓ ህብረት ጋር ለሁለት ዓመታት ያህል ከተነጋገሩ በኋላ የተደረሰውን ሥምምነት ቢቀበል እንደሚያዋጣው ነው ዋናው ተደራዳሪ የመከሩት።
እስካሁን ባለው ጊዜ የብሪታንያ ምክር ቤት ሥምምነቱን ሦስት ጊዜ አልተቀበለውም። ቴሬሳ ሜይ ለአርተኛ ጊዜ ድምፅ እንዲሰጥበት ያቀርባሉ ተብሎ ይጠበቃል።