ቦትሰዋና የእንቅስቃሴ ገደቧን ልታነሳ ነው

  • ቪኦኤ ዜና
ቦትሰዋና

ቦትሰዋና

የኮሮናቫይረስ ስርጭትን ለመቆጣጠር ላለፉት አምስት ሳምንታት የእንቅስቃሴ ገደቦች አጽንታ የከረመችው ቦትሰዋና ከነገ አርብ ጀምራ ቀስ በቀስ መክፈት ልትጀምር መሆኗን ገልጸች።
በሃገሪቱ እስካሁን በቫይረሱ መጠቃቱ የተረጋገጠው ሰው ቁጥር ሃያ ስምንት ሲሆን በበሽታው ህይወቱ ያለፈው አንድ ሰው መሆኑን የቦትሰዋና መንግሥት ገለጿል።