በቦረና በድርቅ የሚሞቱ እንስሳት ቁጥር መጨመሩን ነዋሪዎች ተናገሩ

Your browser doesn’t support HTML5

በቦረና በድርቅ የሚሞቱ እንስሳት ቁጥር መጨመሩን ነዋሪዎች ተናገሩ

በቦረና በድርቅ ሳቢያ የሚሞቱ እንስሳት እየጨመረ መምጣቱ ያሉበትን ችግር እያባባሰ ነው ሲሉ የአሜሪካ ድምጽ ያነጋገራቸው አንዳንድ የአካባቢው ነዋሪዎች ተናገሩ።

በኦሮምያ ክልል ቦረና ዞን የበልግና ክረምት ዝናብ መዘግየቱን ተከትሎ የተከሰተው ድርቅ በርካታ ከብቶችን እየገደለ ነው። በአካባቢው የተከሰተው ድርቅ በሦስት ወራት ውስጥ ብቻ ከዘጠኝ ሺህ በላይ የቤት እንስሳትን መግደሉን ነዋሪዎቹ ተናግረዋል።

መንግሥት ሁኔታውን በአፋጣኝ ካላስተካከለ ችግሩ ከዚህ በላይ ሊባባስ ይችላል ሲሉ ነዋሪዎቹ ገለፀዋል።

ዝርዝሩን ከተያያዘው የድምጽ ፋይል ያድምጡ፡፡