የድርቁ ችግር በቦረና

  • ሔኖክ ሰማእግዜር

በቦረና የደረሰው ድርቅ ላስከተለው የምግብ እጥረት የተጋለጡ የከብት አርቢ ቤተሰብ አባላት

የአሜሪካ ድምፅ ራዲዮ የምሥራቅ አፍሪካን ድርቅና የረሃብ ሁኔታ በቅርብ ይከታተላል፡፡

የአፍሪካ ቀንድን በመታው ድርቅ ዙሪያ በተከታታይ በሚቀርቡት ዘገባዎች ከምንቃኛቸው አካባቢዎች ሪፖርተራችን ሄኖክ ሰማእግዜር ተዘዋውሮ የተመለከታቸው በደቡብ ኢትዮጵያ የቦረና ወረዳዎች ይገኙባቸዋል፡፡

ደቡብ ኢትዮጵያ ሁለት ዓይነት ገፅታዎች ያሏት መሆኑንና የክረምቱ ዝናብ በወቅቱ በጀመረባቸው ከአዋሣ ከተማ በፊትና አልፎም ስፋት ባላቸው አካባቢዎች አዝመራው ከወትሮው እንዳልቀነሰባቸው አርሶ አደሮቹ ገልፀዋል፡፡

ይሁን እንጂ በድርቁ በብርቱ በተመቱት በኦሮሚያ ክልል የቦረና ዞን ቀበሌዎች ውስጥ ከፍተኛ የምግብ እጥረት እንዳለ ተስተውሏል፡፡

ከብት አርቢዎችና ከፊል ከብት አርቢዎች ከሚኖሩባቸው ከአሥራ ሦስቱ የቦረና ቀበሌዎች በተለይ ዲሎ ድሬና ሞያሌ የሚባሉት አካባቢዎች የሚገኙባቸው አምስት ቀበሌዎች ከድርቁ የበረታ ችግር ግንባር ቀደም ተጎጂዎች ናቸው፡፡

ዘጋቢያችን ሄኖክ ሰማእግዜር በአካባቢው ይገኛል፡፡ በድምፅና በምሥል አስደግፎ የላካቸውን ዘገባዎች ተከታተሉ፡፡