የምሥራቅ ቦረና ዞን መዋቅር ውዝግብ በኹሉ አቀፍ ምክክር እንዲፈታ አባ ገዳዎች ጠየቁ

Your browser doesn’t support HTML5

የምሥራቅ ቦረና ዞን መዋቅር ውዝግብ በኹሉ አቀፍ ምክክር እንዲፈታ አባ ገዳዎች ጠየቁ

በኦሮሚያ ክልል የምሥራቅ ቦረና ዞን በዐዲስ መልክ መዋቀሩን ተከትሎ የተፈጠረው ውዝግብ፣ ኹሉንም ባሳተፈ የምክክር መድረክ በሰከነ አካሔድ እንዲፈታ፣ የቦረና እና የጉጂ አባ ገዳዎች ጠየቁ።

የጉጂ አባ ገዳ ጅሎ መንዶ፣ የአስተዳደር መዋቅር መዘርጋት የመንግሥት ሥራ እንደኾነ ገልጸው፣ ለግጭት መንሥኤ እንዳይኾን፣ አቤቱታ አቅርበው እንደነበረ ተናግረዋል። የቦረና አባ ገዳ ኩራ ጃርሶ በበኩላቸው፣ የምሥራቅ ቦረና ዞን መዋቀር፣ ሲነሣ ለቆየው ጥያቄ ምላሽ የሰጠ ቢኾንም፣ ውሳኔውን ተከትሎ የተከሠቱ አለመግባባቶች በምክክር መፈታት እንዳለባቸው አሳስበዋል።

ዝርዝር ዘገባውን ከተያያዘው ፋይል ይከታተሉ፡፡