የቦኮ ሃራም ታጣቂዎች እጅ እንዲሰጡ ጥሪ ቀረበ

ቦኮ ሓራም

የናይጀሪያው የሁከት ቡድን የቦኮ ሃራም ታጣቂዎች እጅ እንዲሰጡ የሃገሪቱ ጦር ጥሪ አሣለፈ፡፡

የጦር ሠራዊቱ ቃል አቀባይ ኮሎኔል ሳኒ ኩካሼካ ኡስማን በሰጡት ቃል የቦኮ ሃራም መደበቂያዎችን ሁሉ የሚያውቁ መሆኑንና ታጣቂዎቹ መከበባቸውን ተናግረዋል፡፡

ጦሩ ማስጠንቀቂያውን ያወጣው ዛሬ የሁከቱ ቡድን ሰሜናዊ ካሜሩን ውስጥ አድርሶታል በተባለ የአጥፍቶ ጠፊ ጥቃት ዘጠኝ ሰው ከተገደለና ሌሎች ሃያ ዘጠኝ ሰዎች ከቆሰሉ በኋላ ነው፡፡

የታጣቂዎቹ አቅም በናይጀሪያ ጦር እጅግ መዳከሙን የተናገሩት ኮሎኔል ኡስማን ይሁን እንጂ ቡድኑ ያለ ለማስመሰል ተመሣሣይ የአጥፍቶ ጠፊ ጥቃቶችን እንደ ዘዴ መያዙን ጠቁመዋል፡፡

ዘገባውን የተያያዘውን የድምጽ ፋይል በመጫን ያዳምጡ።

Your browser doesn’t support HTML5

የቦኮ ሃራም ታጣቂዎች እጅ እንዲሰጡ ጥሪ ቀረበ /ርዝመት - 44ሰ/