ዶ/ር ቦጋለች ገብሬ አረፉ

ቦጋለች ገብሬ

በኢትዮጵያ ልማዳዊ ጎጂ አድራጎቶችን ለማስቀረት ትልቅ አስተዋጸኦ ያደረጉ ዶ/ር ቦጋለች ገብሬ አረፉ።

የሴት ልጅ ግርዛትን ለማስቀረትና የእናቶችና ህፃናት ሞት ለመቀነስ ከፍተኛ አስተዋፅኦ እንዳበረከቱት ዶ/ር ቦጋለች ባደረባቸው ህመም በአሜሪካን አገር ህክምና በመከታተል ላይ እያሉ ነው ከዚህ ዓለም ዛሬ በሞት የተለዩት።

አስክሬናቸው ከሶስት ቀናት በሁዋላ ወደ ኢትዮጵያ እንደሚገባና የቀብር ስነ ስርዓትም በትውልድ አከባቢያቸው እንደሚፍፀም የካምባታና ጣምባሮ ዞን ለቪኦኤ ያስታወቀው።

የተያያዘውን የድምፅ ፋይል ያዳምጡ።

Your browser doesn’t support HTML5

ዶ/ር ቦጋለች ገብሬ አረፉ