ሰማያዊ ፓርቲ በአስቸኳይ ጊዜ አዋጁ ላይ አቤቱታ አሰማ

  • መለስካቸው አምሃ
ሰማያዊ ፓርቲ በአስቸኳይ ጊዜ አዋጁ በቁጥጥር ሥር ውለው ከነበሩ አባላቱና ደጋፊዎቹ መካከል ዛሬም ምንም ዓይነት ውሣኔ ያልተሰጣቸው እንዳሉ አስታወቀ፡፡ ከዘመዶቻቸውም ሆነ ከሕግ ጠበቃዎቻቸው ጋር ስለማይገናኙ ያሉበትን ሁኔታ ለማወቅ መቸገሩንም ፓርቲው ገልጿል፡፡

በጉዳዩ ላይ የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ መርማሪ ቦርዱን ለማነጋገር ያደረግነው ተደጋጋሚ ጥረት አልተሣካም፡፡ የአስቸኳይ ጊዜ አዋጁ ከታወጀ በኋላ ጥቂት የማይባሉ የሠማያዊ ፓርቲ አመራር አባላትና ደጋፊዎች መታሰራቸውን ሰማያዊ ፓርቲ አስታወቀ፡፡

ለተጨማሪ የተያያዘውን የድምፅ ፋይል ያዳምጡ።

Your browser doesn’t support HTML5

ሰማያዊ ፓርቲ በአስቸኳይ ጊዜ አዋጁ ላይ አቤቱታ አሰማ