መኢአድ እና ሰማያዊ የአዲስ አበባን አስተዳደር ከሰሱ

  • መለስካቸው አምሃ

መኢአድ እና ሰማያዊ ፓርቲ

“ዕውቅና ነፍጎናል” ባሉት የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር አንድ አካል ላይ ክሥ መመሥረታቸውን የመላ ኢትዮጵያ አንድነት ድርጅት እና ሰማያዊ ፓርቲ አስታወቁ፡፡

“ዕውቅና ነፍጎናል” ባሉት የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር አንድ አካል ላይ ክሥ መመሥረታቸውን የመላ ኢትዮጵያ አንድነት ድርጅት እና ሰማያዊ ፓርቲ አስታወቁ፡፡

ፓርቲዎቹ ዶሴውን የከፈቱት የፊታችን ዕሁድ፣ መስከረም 28 / 2010 ዓ.ም ሊያካሂዱት የነበረው ሰላማዊ ሰልፍ ዕውቅና ሳያገኝ ከቀረ በኋላ መሆኑን ገልፀዋል።

በጉዳዩ ጣልቃ ገብተው መመሪያ እንዲሰጡም ለጠቅላይ ሚኒስትሩ እና ለአንዳንድ የመንግሥት ከፍተኛ ባለሥልጣናት ደብዳቤ ማስገባታቸውን አመልክተዋል።

ፓርቲዎቹ በጠሩት በዛሬው ጋዜጣዊ መግለጫ ላይ በባህር ዳር ዩኒቨርሲቲ የምህንድስና ተማሪዎች ላይ ተወስዷል ያሉትን “ኢሰብዓዊ” ሲሉ የጠሩትን እርምጃ አውግዘዋል፡፡

ለተጨማሪ የተያያዘውን የድምፅ ፋይል ያዳምጡ።

Your browser doesn’t support HTML5

መኢአድ እና ሰማያዊ የአዲስ አበባን አስተዳደር ከሰሱ